ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በምስራቅ ኮንጎ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት እውቅና መስጠት እንዳለበት የኮንጎ ፕሬዝዳንት አሳሰቡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በምስራቅ ኮንጎ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት እውቅና መስጠት እንዳለበት የኮንጎ ፕሬዝዳንት አሳሰቡ
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በምስራቅ ኮንጎ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት እውቅና መስጠት እንዳለበት የኮንጎ ፕሬዝዳንት አሳሰቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.09.2025
ሰብስክራይብ

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በምስራቅ ኮንጎ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት እውቅና መስጠት እንዳለበት የኮንጎ ፕሬዝዳንት አሳሰቡ

ፌሊክስ ሺሴኬዲ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት፥ "ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሕይወት፣ የተፈጥሮ ሃብትና የሰው ልጆች ፅናት ሀገር ነች። እኛ ለዓለም ሰላም አስተዋጽኦ ማድረግ እንፈልጋለን፤ ነገር ግን ሰላም የሚጀምረው የራሳችንን አሳዛኝ ሁኔታ በመቀበል ነው" ብለዋል።

"በኮንጎ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ላለው የዘር ማጥፋት እውቅና ስጡ። ለእውነት እና ለፍትሕ የምናደርገውን ትግል ደግፉ፤ በአፍሪካ ልብ ውስጥ ዘላቂ ሰላም እንድንገነባ እርዱን" ሲሉም ተማጽነዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፥ "ይህ ግጭት ብቻ አይደለም፤ በኮንጎ ህዝብ ላይ ከ30 ዓመታት በላይ ድምፅ አልባ ሆኖ ሲፈፀም የቆየ የዘር ጭፍጨፋ ነው" ብለዋል።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በምስራቃዊ ግዛቶቿ በሩዋንዳ እና በወኪሎቿ የተፈጸመውን “የዘር ማጥፋት” እውቅና ለማግኘት ዘመቻ የጀመረች ሲሆን፤ ይህንንም ዘመቻ የኪጋሊ መንግሥት “ሞኝነት” ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ሺሴኬዲ "እውነቱን ለማወቅ፣ ለተጎጂዎች ፍትሕ ለመስጠት እና ይህን አሳዛኝ ክስተት ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሲያባብስ የቆየውን የተጠያቂነት እጦት ለማጥፋት" ገለልተኛ ዓለም አቀፍ የምርመራ ኮሚሽን እንዲቋቋም ጠይቀዋል። እንዲሁም በምስራቃዊ ኮንጎ ለተፈጸሙ "የጦር ወንጀሎች፣ በሰብአዊነት ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች እና ለዘር ማጥፋት ወንጀሎች" ተጠያቂ የሆኑ አካላት ላይ የተባበሩት መንግሥታት ማዕቀብ እንዲጥልባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0