የሳሕል ጥምረት ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መውጣት ለሌሎች በር ከፋች ነው - ተመራማሪ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሳሕል ጥምረት ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መውጣት ለሌሎች በር ከፋች ነው - ተመራማሪ
የሳሕል ጥምረት ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መውጣት ለሌሎች በር ከፋች ነው - ተመራማሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.09.2025
ሰብስክራይብ

የሳሕል ጥምረት ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መውጣት ለሌሎች በር ከፋች ነው - ተመራማሪ

ቡርኪና ፋሶ፣ ኒጀር እና ማሊ በተግባራዊ እርምጃዎች የተደገፈ የፓን አፍሪካኒንስት ሐሳቦችን እያቀነቀኑ መታየታቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰላምና ደህንነት ጥናት ተቋም መምህር እና ተመራማሪ ዓለሙ አራጌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ፡፡

“መውጣታቸው ሌሎችን የሚያሳትፍ በር ከፋች አበርክቶ ሊኖረው ይችላል። ምክንያቱም የተወሰኑ ተጨባጭ የፓን ከፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ አንጻር የሚያቀነቅኗቸው ሐሳቦች እና እየወሰዷቸው ያሉ እርምጃዎች አሉ፡፡”

ዓለሙ፣ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች የሚለው መርህ የሚያጎላ አርምጃ መሆኑንም አፅንዖት ሰጥተዋል፡፡

“የአኅጉሪቱ ልጆች ለነሱ ቅርብ በሆኑ ተቋማት እና ለባሕላቸው፣ ለትውፊታቸው፣ ለታሪካቸው ቅርበት ባላቸው አደረጃጀቶች ችግሮችን መፈታት ይሻሉ፡፡”

በምዕራባውያን የሚዘወሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የመሻሻል ነገራቸው እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑ የተለያዩ ሀገራት እንደ ብሪክስ ያሉ አማራጮችን እያማተሩ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0