ኢትዮጵያ፣ ግብፅ በሕዳሴ ግድብ ላይ የምታራምደው አቋም ለብሔራዊ ደህንነቷ ስጋት መሆኑን አስታወቀች
15:51 24.09.2025 (የተሻሻለ: 16:04 24.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ፣ ግብፅ በሕዳሴ ግድብ ላይ የምታራምደው አቋም ለብሔራዊ ደህንነቷ ስጋት መሆኑን አስታወቀች
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞቴዎስ የተፈረመው እና ለተባበሩት መንግሥታት ፀጥታዉ ምክር ቤት መላኩ የተዘገበው ደብዳቤ፣ ግብፅ ኢትዮጵያ ላይ የምታሳየው ዛቻ የአፍሪካ ቀንድን ማተራመስ ቀጣይ ፖሊሲዋ መሆኑ ያሳያል ይላል።
የሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ተመልክቼዋለሁ ያለው ይህ ደብዳቤ፣ የግብፅ ባለሥልጣናት የግድቡን መመረቅ ተከትሎ ለፀጥታው ምክር ቤት የጻፉትን የክስ ደብዳቤ በተመለከተም፣ ኢትዮጵያ ከዓባይ ውኃ የመጠቀም መብቷ ከማንም ፈቃድ መጠየቅ የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም ይላል።
ኢትዮጵያ በትብብር መንፈስ፣ በሙሉ ግልፅነት በመልካም እምነት ላይ የተመሠረተ ቢሆንም፣ ግብፅ ከሰሞኑ ያስገባችው ደብዳቤ ያለ ምንም የትብብር መንፈስ የዓባይን ውኃ በበላይነት በብቸኝነት ለመጠቀም ያሳየችበት ግልፅ ፍላጎት መሆኑንም ደብዳቤው ያስረዳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X