3 ነጥብ 8 ሚሊዮን የወተት ላሞችን በማዳቃል የዝርያ ማሻሻያ መሰራቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
14:59 24.09.2025 (የተሻሻለ: 15:04 24.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
3 ነጥብ 8 ሚሊዮን የወተት ላሞችን በማዳቃል የዝርያ ማሻሻያ መሰራቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘንድሮው ዓመት 5 ሚሊዮን የወተት ላሞች በሰው ሠራሽ ሥነ ዘዴና በመደበኛ መንገድ ለማዳቀል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ አስታውቀዋል።
ይህ እንቅስቃሴ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን ለማሳካት፣ በምግብ ራስን ለመቻልና ስርዓተ ምግብን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እያበረከተ ነው ብለዋል።
በዶሮና በንብ ዕርባታ ላይም አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ሚኒስትር ዲኤታው በዘንድሮው ዓመት በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በምዕራብ አርሲ ዞን በሰው ሠራሽ ሥነ ዘዴ የማደቀል ሥራ መጀመሩ የዕቅዳችን አንዱ አካል ነው ብለዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X