በሀገር አቀፍ ደረጃ 130 የጤና ተቋማት ኤሌክትሮኒክ የህክምና መረጃ ሥርዓትን መተግበር ጀምረዋል - ጤና ሚኒስቴር
20:56 23.09.2025 (የተሻሻለ: 21:04 23.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሀገር አቀፍ ደረጃ 130 የጤና ተቋማት ኤሌክትሮኒክ የህክምና መረጃ ሥርዓትን መተግበር ጀምረዋል - ጤና ሚኒስቴር
የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን እንደ ሀገር የአሥር ዓመት ስትራቴጂ ተቀርፆ እየተተገበረ ይገኛል፤ በዚህም 48 የሚሆኑት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ከወረቀት ንክኪ የሆነ አገልግሎት እየሰጡ ነው ሲሉ በሚኒስቴሩ የዲጅታል ጤና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ ገመቺስ መልካሙ ተናግረዋል።
አክለውም የዲጂታል መረጃ ስርዓቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰቡ የጤናና የህክምና መረጃዎችን በማደራጀት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ስለመሆኑ አመልክተዋል ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ስራ አስፈጻሚው አያይዘውም እንደሀገር የዲጅታል ጤና አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ተቋማት ከፍተኛ የአገልግሎት ለውጥ እና የአሰራር ቅልጥፍና እያስመዘገቡ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X