"አፍሪካ የጋራ ተግባራትን መቀበል እና የራሷን ኢንዱስትሪዎች መገንባት አለባት" ሲሉ ፕሬዝደንት ቲኑቡ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"አፍሪካ የጋራ ተግባራትን መቀበል እና የራሷን ኢንዱስትሪዎች መገንባት አለባት" ሲሉ ፕሬዝደንት ቲኑቡ ተናገሩ
አፍሪካ የጋራ ተግባራትን መቀበል እና የራሷን ኢንዱስትሪዎች መገንባት አለባት ሲሉ ፕሬዝደንት ቲኑቡ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.09.2025
ሰብስክራይብ

"አፍሪካ የጋራ ተግባራትን መቀበል እና የራሷን ኢንዱስትሪዎች መገንባት አለባት" ሲሉ ፕሬዝደንት ቲኑቡ ተናገሩ

የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት በ80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጎን ለጎን በኒውዮርክ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የማዕድን ስትራቴጂ ቡድን ከፍተኛ ደረጃ የውይይት መድረክ ላይ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼቲማ ተወክለው እንደተናገሩት፤ አህጉሪቱ “በራሷ እግር መቆም” እና ራሷን መደገፍ አለባት።

ከፕሬዝዳንቱ መግለጫ የተወሰዱ ዋና ዋና ሀሳቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

አፍሪካ ሃብቷን ለመጠበቅ እና በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ የጋራ አቅም ለመፍጠር በአንድነት መስራት አለባት።

የማዕድን ኢኮኖሚው ለአህጉሪቱ ጥቅም በሚያስገኝ መልኩ ሊለማ ይገባል።

የተጠናቀቁ ምርቶችን የማስመጣት "አሳፋሪ ዑደት" ማብቃት ስላለበት ኢንዱስትሪዎች በአፍሪካ አፈር ላይ መገንባት አለባቸው።

ከአፍሪካ የጂኦሎጂ ሀብት ጋር የተያያዙ መረጃዎች በአፍሪካ ማዕድናት እና የኃይል ሀብት ምደባ እንዲሁም በፓን-አፍሪካ የሀብት ሪፖርት ማቅረቢያ ኮድ በኩል በአፍሪካውያን ባለቤትነት ስር ይሆናሉ፤ ይደራጃሉ እና ደረጃቸውን የጠበቁ ይሆናሉ።

በመንግስት የሚመራው የማዕድናት ፍለጋ ማፋጠን አለበት።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0