ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች፦

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች፦
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች፦ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.09.2025
ሰብስክራይብ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች

አሜሪካ በባደን የስልጣን ዘመን የነበረውን "የአራት ዓመታት መንግሥታዊ አክራሪነትን" ማሸነፏን እና ዛሬ አገሪቱ ዓለም አቀፍ ተፎካካሪ እንደሌላት ገልጸዋል፤ ኔቶም ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ እንደሆነ ተናግረዋል።

አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት ከህገ-ወጥ ስደት ጋር በተመሳሳይ ፈተናዎች እንደሚገጥሟቸው እና እርምጃ ከመውሰድ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው ጠቅሰዋል። "ስደተኞችን ከመጠን በላይ በመቀበል ላይ ያሉ አገራት ወደ ሲኦል እየሄዱ ነው" ሲሉም አክለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ ግጭቶችን በመፍታት ረገድ ውጤታማ አይደለም።

በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ "በከፍተኛ ወጪ መጨመር" የሚመጣ ብክነት አለ፤ ድርጅቱ በሀብት አያያዝ ደካማ መሆኑን ገልፀዋል።

በጋዛ ያለው ጦርነት በአስቸኳይ ማብቃት እና የቀሩትም ታጋቾችም መልቀቅ አለባቸው።

አውሮፓ ከሩሲያ የኃይል ሀብቶችን መግዛቷን ከቀጠለች ሩሲያን መዋጋት እንደማትችል ገልጸዋል፤ ይህም አሳፋሪ ነው ብለዋል።

ትራምፕ ቻይና እና ህንድ ከሩሲያ ጋር ባላቸው ኢኮኖሚያዊ ትብብር ምክንያት የዩክሬን ግጭት "ዋና የገንዘብ ምንጮች" ብለዋቸዋል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የባዮሎጂካል ጦር መሳሪያ ልማትን ሙሉ በሙሉ ማስቆም አለበት።

አሜሪካ በአዲስ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረተ የማረጋገጫ ስርዓት በመጠቀም ባዮሎጂካል የጦር መሳሪያዎችን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ትመራለች።

ትራምፕ የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ የሚነሱ መላምቶች የምንግዜም ትልቁ ውሸት እንደሆኑ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0