“የሱዳን ቀውስ ቅርምት” ምዕራባውያን በዩክሬን ግጭት ውስጥ ያላቸውን ሚና ለመደበቅ ያለመ ነው - የቡርኪና ፋሶ የፖለቲካ ተንታኝ
18:05 23.09.2025 (የተሻሻለ: 18:14 23.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“የሱዳን ቀውስ ቅርምት” ምዕራባውያን በዩክሬን ግጭት ውስጥ ያላቸውን ሚና ለመደበቅ ያለመ ነው - የቡርኪና ፋሶ የፖለቲካ ተንታኝ
የአዘርባጃን የጦር መሳሪያ አምራቾች በሱዳን በኩል ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እያቀረቡ ነው የሚሉ ዘገባዎች ይህን ስትራቴጂ የሚያንጸባርቁ ናቸው ሲሉ ሊያንሁዌ ኢምሆቴፕ ባያላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
“በዚህ የጦር መሳሪያ ዝውውር ውስጥ ተባባሪ የሆኑ ሁሉም ሀገራት የሰላም ወዳጅ ወይም ዓለም አቀፍ ሕግን አክባሪ ሆነው አያውቁም” ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል።
እንደ እሳቸው ገለጻ፤ "በሊቢያ ሁከትን የፈጠሩት አርክቴክቶች" አሁን የፈጠሩትን ትርምስ ለመጠቀም "ትኩረታቸውን ወደ ሱዳን ቀይረዋል"።
ባያላ አክለውም እንደ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር ያሉ ሀገራት "በግዴለሽነት ወደ ዩክሬን በሚገቡ የጦር መሳሪያዎች ይሰቃያሉ፤ ምክንያቱ ደግሞ እነዚህ መሳሪያዎች በተለያዩ መንገዶች ወደ ሳህል አካባቢ ይደርሳሉ"።
በተጨማሪም እነዚህ የጦር መሳሪያዎች "በፈጥኖ ደራሽ አማፂያን እጅ ውስጥ ቢወድቁ" ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ይህ ከተከሰተ የሱዳን ግጭት "እጅግ በጣም አሳሳቢ እና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ መልክ ይይዛል" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X