የአዳማ-አዋሽ ፈጣን መንገድ ግንባታን ማስጀመሪያ የ181 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ድርድር ተጠናቀቀ
13:32 23.09.2025 (የተሻሻለ: 13:34 23.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአዳማ-አዋሽ ፈጣን መንገድ ግንባታን ማስጀመሪያ የ181 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ድርድር ተጠናቀቀ
ግንባታውን አስመልክቶ በአፍሪካ ልማት ባንክ፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር መካከል የመጨረሻው የገንዘብ ድጋፍ ድርድር ተድርጓል።
ይህ ድርድር ባንኩ ፕሮጀክቱን በቅርቡ ለቦርዱ አቅርቦ እንዲያፀድቅ ያስችለዋል፡፡ ለፕሮጀክቱ በአጠቃላይ የተያዘው የበጀት ድልድል የሚከተለውን ይመስላል።
181.5 ሚሊዮን ዶላር በአፍሪካ ልማት ባንክ ብድር እንደሚሸፈን ይጠበቃል። (የመጀመሪያው 48 ኪሜ)
19 ኪሎ ሜትር መንገድ ደግሞ በኮሪያ ኤግዚም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግለት ታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ 34.2 ሚሊዮን ዶላሩን ለመሸፈን አቅዷል።
ይህ መንገድ ኢትዮጵያን፣ ጅቡቲን እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኝ ትልቅ ፕሮጀክት ሲሆን፣ የፋይናንስ ስምምነቱ እ.አ.አ. በ2026 መጀመሪያ ላይ ተፈርሞ ግንባታው ወደ ትግበራ ይገባል ተብሎ ታቅዷል ሲሉ የግል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X