'ከ10 ዓመታት በኋላ ገቢያችንን 25 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል' - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
12:07 23.09.2025 (የተሻሻለ: 12:14 23.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
'ከ10 ዓመታት በኋላ ገቢያችንን 25 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል' - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ በእ.ኤ.አ በ2035፣ 209 ዓለም አቀፍ እና 31 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዲሁም 271 አውሮፕላኖች እንደሚኖሩት መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
አየር መንገዱ እቅዱን ለማሳካት ከሚያደርጋቸው የማስፋፊያ ሥርዎች በተጨማሪ
67 ነጥብ 2 ሚሊዮን መንገደኞችንም በማጓጓዝ ገቢውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ፣
አሁን ላይ በረራ ከሚያደርግባቸው አምስቱ አኅጉራት በተጨማሪ አውስትራሊያንም መጨመር፣
ብዛት ባላቸው ሀገራት የበረራ መጠኑን ከአንድ በላይ እስከ አራት ጊዜ ለማድረግ እና
በየዓመቱ 300 ፓይለት ለማሠልጠን እቅድ ይዟል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X