የሱዳን ጦርነት ተበዝብዟል፤ አፍሪካ ለኔቶ የውክልና ጦርነቶች የጦር ሜዳ መሆን የለባትም ሲሉ ተመራማሪው ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሱዳን ጦርነት ተበዝብዟል፤ አፍሪካ ለኔቶ የውክልና ጦርነቶች የጦር ሜዳ መሆን የለባትም ሲሉ ተመራማሪው ተናገሩ
የሱዳን ጦርነት ተበዝብዟል፤ አፍሪካ ለኔቶ የውክልና ጦርነቶች የጦር ሜዳ መሆን የለባትም ሲሉ ተመራማሪው ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.09.2025
ሰብስክራይብ

የሱዳን ጦርነት ተበዝብዟል፤ አፍሪካ ለኔቶ የውክልና ጦርነቶች የጦር ሜዳ መሆን የለባትም ሲሉ ተመራማሪው ተናገሩ

“ይህ በጣም አሳዛኝ ነገር ነው። የአፍሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት በኔቶ ተበዝብዞ የዩክሬን ግጭት እንዲቀጥል እየተደረገ ነው። በዚህ ሂደትም የአፍሪካ ሉዓላዊነት ወይም የቀረው ትንሽ የሉዓላዊነት ክፍል በእጅጉ እየተናደ ነው” ሲሉ የጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ዶክትሬት ተመራማሪ የሆኑት ሲዞ ንካላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ወደ ዩክሬን የጦር መሣሪያ ለማዘዋወር እንደ መሸፈኛነት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፤ በሚለው ዘገባ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ንካላ እንዲህ ዓይነቱ እቅድ የሱዳንን ቀውስ ከማባባስም በላይ በመላው አኅጉሪቱ ውስጥ  አለመረጋጋትን እንደሚያባብስ አስጠንቅቀዋል።

“ከጦር መሣሪያዎቹ አንዳንዶቹ በእርግጠኝነት በአማፂያን እጅ ውስጥ ይወድቃሉ፤ እነርሱም ንጹሐን ዜጎችን ለማሸበር ይጠቀሙበታል። በሳሕል ቀጣና ውስጥ አለመረጋጋት ለረጅም ጊዜ የዘለቀበት ምክንያት ይህ ነው፤ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በቀጣናው ውስጥ ያሉትን የሽብር እንቅስቃሴዎች እያነቃቃና ትስስራቸውን እያሳደገ ስለሆነ።”

ንካላ ይህንን ጉዳይ “በጣም አደገኛ ማሳያ” ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ የዚህ ሴራ መጋለጥ እንደ ትልቅ ለውጥ መታየት አለበት ሲሉ ተከራክረዋል።

“አፍሪካ ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ግጭቶች በውጭ አካላት የገንዘብ ድጋፍና እገዛ እንደሚደረግላቸው ከረጅም ጊዜ በፊት ሲዘገብ ቆይቷል። ይህ ዘገባ እንደዚህ ያሉትን ጥያቄዎች የሚያረጋግጥ ነው። በእኔ እይታ አሁን ያለው አስፈላጊ ነገር ይህ ሴራ መጋለጡ ነው። ይህንን ለማስቆም አንድ ነገር ማድረግ የአፍሪካ መሪዎች ተግባር ነው።”

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0