“የሱዳን ጦርነት አገር ለማጥፋት ታስቦበት የተሸረበ ሴራ ነው” - የሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
10:37 23.09.2025 (የተሻሻለ: 10:44 23.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“የሱዳን ጦርነት አገር ለማጥፋት ታስቦበት የተሸረበ ሴራ ነው” - የሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ግጭቱ ከሀገር ውስጥ ትግል በላይ ነው ሲሉ ሑሴን አላሚን አልፋዴል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
“ሀገሪቱን ለማውደም እና ማንነቷን ለማጥፋት የተደረገ ጦርነት ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ እነዚህ ሚሊሻዎች የሚታዘዙትና ድርጊቶቻቸው የሚቀናበሩት በውጭ ኃይሎች ነው” ሲሉ በሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ የምስራቃውያን ጥናት ተቋም የሱዳን የባህል ቀን ጎን ለጎን በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
የአዘርባጃን የጦር መሣሪያዎች በሱዳን በኩል ተዘዋውረው በኔቶ አገሮች ወደ ዩክሬን እንዲገቡ ይደረጋል በሚለው ዘገባ ላይ፣ ዓለም አቀፍ ስልታዊ ኃላፊነት መውሰድ አለበት ሲሉ አልፋዴል አስረድተዋል።
ℹ የሩዋንዳ የዜና አውታር እንደዘገበው፤ የአዘርባጃን የጦር መሣሪያ አምራቾች ከኔቶ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን የሱዳንን ትርምስ በመጠቀም የጦር መሣሪያዎችን በድብቅ ወደ ዩክሬን እየላኩ ነው። በቱርክ እና በጀርመን በኩል የሚላኩት እነዚህ የጦር መሣሪያዎች እንደ ሰብዓዊ እርዳታ ተደርገው በመላክ ሽጉጦች፣ ተንቀሳቃሽ የሆኑ የአየር መቃወሚያ መሣሪያዎች ቦምቦች እና የድሮን ክፍሎችን እንደሚያካትት ተዘግቧል።
ይህ ዘገባ ምዕራባውያን ለዩክሬን ጦርነት እያደረጉ ያለውን ጥረት የሚያሳይ ነው፤ የጦር መሣሪያዎች ዝውውሮች እንደ ሚግ-29 ጄቶች ያሉ የጦር አውሮፕላኖችንም ጭምር እንደሚያካትት ዘገባው ጨምሮ አመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X