ሩሲያ የ”ኒው ስታርት” ስምምነት ገደቦችን የኑክሌር ውይይት እንዲቀጥል ለማድረግ ስትል አራዝማለች - ተንታኝ

ሩሲያ የ”ኒው ስታርት” ስምምነት ገደቦችን የኑክሌር ውይይት እንዲቀጥል ለማድረግ ስትል አራዝማለች - ተንታኝ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን *የኒው ስታርት ስምምነት ገደቦችን ለማራዘም ያቀረቡት ሐሳብ ሁኔታዎች የተረጋጉ ከሆኑ ሩሲያ የመታዘዝ ይሁንታ እንዳላት ያሳያል ሲሉ በሞስኮ የሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ የዓለም ኢኮኖሚ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተቋም ባልደረባ ዲሚትሪ ስቴፋኖቪች ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
እሳቸው እንደጠቀሱት፣ ስምምነቱ በየካቲት 2026 ከማብቃቱ በፊት ለድርድር ዕድል አለ፡፡ የአንድ ዓመት የጊዜ ገደቡም “የቀድሞው የትራምፕ አስተዳደር የኑክሌር ጦር መሣሪያዎችን ለአንድ ዓመት ለማቆም ያቀረበውን ሐሳብ የሚያስተጋባ ነው” ብለዋል።
ይህ እርምጃ የሩሲያ ስትራቴጂያዊ ኃይሎች ለጦርነት ስንዱ እንደሆኑ እና ሞስኮ “በማንኛውም የፀጥታ ሁኔታ ለውጥ ውስጥ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ወይም በወታደራዊ-ቴክኒካዊ ዘዴዎች ለመንቀሳቀስ ዝግጁ መሆኗን” ይጠቁማል።
ባለሙያው “የአሜሪካ ምላሽ አዎንታዊ፣ አሉታዊ ወይም ከቁብ የማትቆጥረው ሊሆን ይችላል” ይላሉ፡፡
ፕሬዝዳት ትራምፕ ጉዳዩን ለመመልከት ፍላጎት አላቸው፡፡
በአሜሪካ ያሉ ተከፋይ ጉዳይ አስፈጻሚዎች (ሎቢስት) በቻይና እና ሩሲያ ስጋት በሚል ለማባባስ ግፊት እያደረጉ ነው፡፡
ስቴፋኖቪች እንደገለፁት፣ የአሜሪካ ምላሽ በውስጥ ፖለቲካዋ፣ በራሷ ስትራቴጂያዊ የማጥቃት የጦር መሣሪያዎች መረሃ ግብሮች ሂደት እና አዳዲስ ሥርዓቶችን የማሰማራት ፍጥነት ላይ የሚወሰን ነው።
*ኒው ስታርት በሩሲያ እና አሜሪካ መካከል የኑክሌር ጦር መሣሪያን ለመቀነስ በጎርግሮሳውያኑ 2010 ተፈርሞ በ2011 ወደ ትግበራ የገባ ስምምነት ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X