ብሪክስ የአባል አገራቱን የአቪዬሽን ዘርፍ ለማሳደግ ተጨማሪ አቅም ይሆናል - የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

ሰብስክራይብ

ብሪክስ የአባል አገራቱን የአቪዬሽን ዘርፍ ለማሳደግ ተጨማሪ አቅም ይሆናል - የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

ላዕከ ታደሰ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ብሪክስ በሥልጠና፣ በዕውቀት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር የአባል አገራቱን የአቪዬሽን ዘርፍ ለማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ ሊያደርግ እንደሚችል ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፎ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ብቁ የአቪዬሽን ባለሙያዎችን በማፍራት ላይ መሆኗንም አንስተዋል።

"ሥልጠና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕድገት አንዱ አካል ነው። የሚያስፈልገንን የሰው ኃይል በራሳችን ከማሟላት ባሻገር፣ ለአፍሪካ ወንድሞቻችን የአቪዬሽን ባለሙያዎችን በማፍራት በሥልጠና ረገድ በራሳችንን የምንተማመን ሆነናል" ብለዋል።

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሰቲ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሳምነት 1 ሺ 103 ሰልጣኞችን በተለያዩ መስኮች ማስመረቁ ይታወሳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0