ምዕራባውያን ለርካሽ የጦር መሣሪያ ምርት ሲሉ በቀውስ ውስጥ ያሉ ሀገራትን ይበዘብዛሉ ሲሉ ሊባኖሳዊዉ ባለሙያ ተናገሩ
17:44 22.09.2025 (የተሻሻለ: 17:54 22.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ምዕራባውያን ለርካሽ የጦር መሣሪያ ምርት ሲሉ በቀውስ ውስጥ ያሉ ሀገራትን ይበዘብዛሉ ሲሉ ሊባኖሳዊዉ ባለሙያ ተናገሩ
"በአፍሪካ ያለው ጥቁር ገበያ በአንድ በኩል የውስጥ ግጭቶችን ለማቀጣጠል እና በሌላ በኩል ደግሞ መሣሪያዎችን ወደ ዩክሬን ለማስተላለፍ ያገለግላል" ሲሉ የሊባኖሱ ባለሙያ ባሻር ሳሊባ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ሳሊባ ይህን ያሉት የአፍሪካ ጥቁር ገበያ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ለማቅረብ እየዋለ ነው በሚል በቀረበው ዘገባ ላይ በሰጡት አስተያየት ነው።
ተንታኙ እንዳመለከቱት የአውሮፓ ታክስ ከፋዮች የጦር መሣሪያዎቹ በአካባቢው የሚመረቱ እንደሆኑ እንዲያስቡ ይደረጋሉ፤ ነገር ግን መሣሪያዎቹ የሚመነጩት የኢኮኖሚ እና የፀጥታ ቀውስ አጋጥሟቸው ያልተረጋጉ ሀገራትን በመበዝበዝ ነው።
“ምዕራባውያን የራሳቸውን ፍላጎት ለማሳካት ከሚሄዱባቸው ወገንተኛ መንገዶች አልፈው በመሄድ፣ ለሚለዋወጡ ፍላጎቶቻቸው የሚስማሙ ብዙ ደረጃዎችን መጠቀም ጀምረዋል” ብለዋል።
ራሳቸው ን የቻሉ የአፍሪካ ሀገራት ከዚህ የበላይነት አሰራር ለመላቀቅ ይፈልጋሉ፤ ነገርግን እንደ ሱዳን ያሉ የተበታተኑ ሀገራት ግን “ለጣልቃ ገብነት ክፍት መድረክ” ሆነው ይቆያሉ ሲሉ አብራርተዋል።
“አዘርባጃን እራሷ በዚህ ምዝበራ ውስጥ መጠቀሚያ እየሆነች ነው፡፡ ይህም የማያዋጣ ስትራቴጂካዊ ቁመና እንድትይዝ ያደርጋታል። ከተጨማለቀ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር እቅዶች ይልቅ አስፈላጊ እና ትርፋማ የሆነው ከሩሲያ ጋር ያላት ግንኙነት ይሻላታል” ሲሉ ሳሊባ ተናግረዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X