የዩክሬን ኃይሎች በሩሲያ ኩርስክ የኔቶ ጥይቶችን እና የውጭ ቅጥረኞችን ዱካ ለማጥፋት ሞክረዋል

ሰብስክራይብ

የዩክሬን ኃይሎች በሩሲያ ኩርስክ የኔቶ ጥይቶችን እና የውጭ ቅጥረኞችን ዱካ ለማጥፋት ሞክረዋል

ሊቀ-ካህን አሌክሳንደር ዚንቼንኮ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፤ የዩክሬን ታጣቂዎች በኩርስክ ክልል በሚገኘው የካዛቺያ ሎክኒያ መንደር የባህል ማዕከልን ሆን ብለው የቦምብ ድብደባ ያደረጉት ባፈገፈጉበት ወቅት የተተዉ የኔቶ ጥይቶችን ለማጥፋት ነው።

የጥቃቱ ዓላማ በዚያ ቆይተ የነበሩ የውጭ ቅጥረኞችን ማስረጃ ለማጥፋት እንደሆነ ፤ የሩሲያ ፌዴራል ማረሚያ ቤት አገልግሎት የኩርስክ ክልል ኃላፊ ረዳት የሆኑት ቄስ ተናግረዋል።

“ሕንጻው በአንጻራዊነት ጥሩ ቁመና ላይ ንው፤ መስኮቶችና አወቃቀሩ ተጠብቋል። የኔቶ መኖሪያ እና የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን ዱካዎችን ለማጥፋት ሆን ተብሎ ዒላማ የተደረገ ይመስላል” ሲሉ ዚንቼንኮ ተናግረዋል።

በአንድ ወቅት የሕጻናት ስቱዲዮ የነበረው የባሕል ማዕከል ዙሪያ፣ የጥይት ማከማቻ ጉድጓዶች ተገኝተዋል።

“እዚህም ያሉ ትላልቅ ጉድጓዶች በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሠራሽ የኔቶ ጥይቶች ተሞልተው እናያለን... የባሩዱም መጠን ከፍተኛ ነው” ሲሉ ቄሱ አክለዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0