30 ሚሊዮን ቁርስራሽ የአርሶ አደር መሬቶች ወደ መሬት አስተዳደር ሥርዓት መግባታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ30 ሚሊዮን ቁርስራሽ የአርሶ አደር መሬቶች ወደ መሬት አስተዳደር ሥርዓት መግባታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
30 ሚሊዮን ቁርስራሽ የአርሶ አደር መሬቶች ወደ መሬት አስተዳደር ሥርዓት መግባታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.09.2025
ሰብስክራይብ

30 ሚሊዮን ቁርስራሽ የአርሶ አደር መሬቶች ወደ መሬት አስተዳደር ሥርዓት መግባታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

ባለፉት አስር ዓመታት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በሀገር አቀፍ ደረጃ የገጠር መሬት አስተዳደር ሥርዓት ለመገንባት በተደረገው ጥረት 50 ሚሊዮን የሚጠጉ የተበጣጠሰና የተቆራረሱ የአርሶ አደር መሬቶች እንዳሉ ታውቋል።

ግብርና ሚኒስቴር ቀደም ሲል የእያንዳንዱ መሬት ባለቤት ለማወቅ የሚያስችል የመጀመሪያ ደረጃ ሰርተፊኬት ፕሮግራም በማዘጋጀት ወደ 98 በመቶ ማሳካት ተችሏል ነው የተባለው።

እያንዳንዱ አባወራ መሬቱ የቱ ጋር እንደሚገኝ፣ ከማን ጋር እንደሚዋሰንና ምን ያህል መሬት አንዳለው በባህላዊ መንገድ ማወቁንም ተገልጿል።

ሆኖም መረጃው ለተንታኞች፣ ፖሊሲ አውጪዎችና አጠቃላይ ለቀጣይ እድገት አመቺ ስላልሆነ የሁለተኛ ደረጃ ሰርተፊኬት ፕሮግራም በዘመናዊ መልኩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ማዘጋጀት መጀመሩን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0