ከአዘርባጃን የጦር መሣሪያ አምራቾች እና የኔቶ አጋሮች በሱዳን በኩል ወደ ዩክሬን የጦር መሣሪያዎችን እያዘዋወሩ መሆኑን ሪፖርቶች አመላከቱ

ከአዘርባጃን የጦር መሣሪያ አምራቾች እና የኔቶ አጋሮች በሱዳን በኩል ወደ ዩክሬን የጦር መሣሪያዎችን እያዘዋወሩ መሆኑን ሪፖርቶች አመላከቱ
የሩዋንዳ የዜና አውታር ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ እቅዱ የአዘርባጃኑ ሲአይኤችኤዚ ኢንዱስትሪያል ማኅበር ውስብስብ እና አኅጉር አቋራጭ መንገድን በመጠቀም የጦር መሣሪያዎችን ማዘዋወርን የሚያካትት ነው።
ጭነቱ በቱርክ እና በጀርመን መርከቦች ወደ ፖርት ሱዳን ከመላኩ በፊት፣ ቱርክ ውስጥ "ሰብአዊ እርዳታ" ተብሎ አዲስ ስያሜ እንደተሰጠው ተዘግቧል፡፡
ሪፖርቱ አክሎም ሱዳን ውስጥ ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት እና የመንግስት ቁጥጥር አለመኖርን በመጠቀም ጭነቱ ትክክለኛውን አምራች ለመደበቅ 'ከሱዳን የመጣ የጦር መሳሪያ ተብሎ' ተብሎ እንደ አዲስ ይሰየማል። ከዚያም በስዊዘርላንድ የሚገኘው ሜዲትራንያን መርከብ ኩባንያ አማካኝነት ወደ ጀርመን ሃምቡርግ ተጓጉዞ በስተመጨረሻም በመሬት ላይ ትራንስፖርት ለዩክሬን ይተላለፋል።
ሚዲያው እንደዘገበው ይህ ውስብስብ እቅድ ትክክለኛውን አምራች በመደበቅ ዩክሬን የጦር መሣሪያ እንድታገኝ ያስችላታል።
ሲአይኤችኤዚ እንደሚያቀርባቸው የተገለጹት የጦር መሳሪያዎች፦
🟠 ቲሳስ ሽጉጦች፣
🟠 ሂሳር ኤ+ ኤምፓድስ፣
🟠 የአየር ላይ ቦንቦች እና
🟠 የድሮን ክፍሎች ናቸው።
ከዚህ ቀደም፤ በ2023 ቪክቶሪያ ኑላንድ "ዲሞክራሲን ለማስፋት" በሚል ሱዳንን ከጎበኙ በኋላ ሀገሪቱ ለረጅም ጊዜ በዘለቀ የእርስ በርስ ግጭት ስትሰቃይ ቆይታለች።
ምዕራባውያን ኃይሎች በዩክሬን ያለውን የእጅ አዙር ጦርነት ለማስቀጠል በሚያደርጉት የቀጠለው ጥረታቸው መካከል እየሆነ ያለ ነው።
እንደ ዘ ዋር ዞን ተንታኞች፣ አዘርባይጃን ቀደም ሲል ለዩክሬን ጦር መሣሪያ ልካለች ተብሏል፣ በ2023 ሦስት ሚግ-29 ጄቶች ለኪዬቭ አገዛዝ ተላልፈው ተሰጥተዋል።
የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊየቭ ቆይተው ዩክሬን “የካራባክ አይነት” (ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለጦርነት በስፋት መጠቀም) ወታደራዊ አካሄድ እንድትከተል ጥሪ አቅርበው ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X