አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎዳና ላይ የብስክሌት የዓለም ሻምፒዮና ማስተናገድ ጀመረች
11:02 22.09.2025 (የተሻሻለ: 11:04 22.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎዳና ላይ የብስክሌት የዓለም ሻምፒዮና ማስተናገድ ጀመረች
የሩዋንዳዋ ኪጋሊ ከመስከረም 11 እስከ 18 ዓለም አቀፉ የብስክሌተኞች ሕብረት ያዘጋጀውን ሻምፒዮና በማስተናገድ ላይ ትገኛለች።
በዓለም አቀፉ የብስክሌት ሕብረት መረጃ መሠረት 36 የአፍሪካ ሀገራት በብስክሌት ፍልሚያው ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከእነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ሀገራት ተካትተዋል፦
አልጄሪያ
ቤኒን
ቡርኪና ፋሶ
ቡሩንዲ
ካሜሩን
ኮሞሮስ
ጋቦን
ጋምቢያ
ጊኒ
ማዳጋስካር
ማሊ
ሞሮኮ
ኒጀር
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ
ሴኔጋል እና
ቱኒዚያ ይጠቀሳሉ።
በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ 108 ሀገራት እና 769 ተወዳዳሪዎች መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል።
በሻምፒዮናው መርሃ ግብር ውስጥ የሴቶች እና የወንዶች የጊዜ ገደብ ውድድሮች፣ የቡድን ቅብብል ውድድሮች እና የጎዳና ላይ ውድድሮች ተካትተውበታል፡፡ እነዚህ ውድድሮች 1 ሺህ 771 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ተራራን መውጣትን የመሳሰሉ ፈታኝ የሆኑ መሰናክሎችን ያካተቱ ናቸው።
የውድድር ምድቦቹ የጀማሪ፣ ከ23 ዓመት በታች እና የመደበኛ ተወዳዳሪዎች ምድቦችን ያካተቱ ሲሆን፤ የሴቶች ከ23 ዓመት በታች ምድብ በ2023 ለመጀመሪያ ጊዜ መታከሉ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/ © telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ