የማላዊ ምርጫ፦ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በመምራት ላይ እንደሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ሪፖርት ጠቆመ
19:28 21.09.2025 (የተሻሻለ: 19:34 21.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የማላዊ ምርጫ፦ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በመምራት ላይ እንደሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ሪፖርት ጠቆመ
ከአንድ አራተኛ የምርጫ ክልሎች የተገኙ ጊዜያዊ ውጤቶች ፒተር ሙታሪካ በ51 በመቶ ድምፅ እንደሚመሩና ሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ በ39 በመቶ ድምፅ እየተከተሉ እንደሆነ አሳይተዋል።
አንድ እጩ የመጀመሪያውን ዙር ለማሸነፍ ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ማግኘት ይኖርበታል። ይህ የማይሆን ከሆነ ከሁለቱ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙ ተወዳዳሪዎች መካከል ሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ምርጫ ይካሄዳል።
የማላዊ ዜጎች መስከረም 6 አዲስ ፕሬዝዳንት እና የብሔራዊ ምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ ድምፃቸውን ሰጥተዋል። የሀገሪቱ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻውን ውጤት መስከረም 14 እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X