ኬንያዊው አትሌት አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ በሞስኮ ማራቶን ድል ተቀዳጀ

ሰብስክራይብ

ኬንያዊው አትሌት አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ በሞስኮ ማራቶን ድል ተቀዳጀ

አልፎንስ ኪቢዎት ኪገን የ42 ኪሎ ሜትሩን ውድድር አስደናቂ በሆነ 2 ሰዓት፡ 9 ደቂቃ፡ 31 ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት አጠናቋል።

ውጤቱ እ.ኤ.አ በ2024 በሞሮኳዊው ዩነስ ቤናር ተመዝግቦ የነበረውን 2 ሰዓት፡ 11 ደቂቃ፡ 34 ሰከንድ የሞስኮ ማራቶን ሰዓት አሻሽሏል።

ኢትዮጵያዊው ገብረፃዲቅ አብራሃ ከኪገን በ38 ሰከንድ ዘግይቶ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። የ2023 የሞስኮ ማራቶን አሸናፊ ሩሲያዊው ዲሚትሪ ኔዴሊን ከመሪው በ1 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ ዘግይቶ በሶስተኛነት አጠናቋል።

በሴቶች ውድድር ሩሲያዊቷ ሉይዛ ሌጋ በ2 ሰዓት፡ 28 ደቂቃ፡ 32 ሰከንድ አንደኛ በመውጣት የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0