ኢትዮጵያ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ለማዘጋጀት ጥያቄ አቀረበች
15:57 20.09.2025 (የተሻሻለ: 16:04 20.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ለማዘጋጀት ጥያቄ አቀረበች
ሻምፒዮናውን ለማዘጋጀት ፍላጎት ላላቸው ሀገራት በጃፓን ቶኪዮ በተዘጋጀው መርሃ-ግብር ከመንግሥትና ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተወጣጡ አመራሮች ተካፍለዋል።
ኢትዮጵያ ለአትሌቲክሱ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ ችግሮችን በመቅረፍ እና በቂ ስታዲዬሞችን በመገንባት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም መፍጠሯን ገልፀዋል።
ሀገሪቱ በ2029 ወይም በ2031 የሚካሄደውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለማሠናዳት ነው ለዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጥያቄውን ያቀረበችው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X