ሮሳቶም የኢትዮጵያን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠ
12:58 20.09.2025  (የተሻሻለ: 13:04 20.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
 / ሰብስክራይብ
ሮሳቶም የኢትዮጵያን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠ
በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ከሩሲያ መንግሥት ኮርፖሬሽን ሮሳቶም ምክትል ዳይሬክተር ኒኮላይ ስፓስኪ ጋር ትናንት መገናኘታቸውን ኤምባሲው ይፋ አድርጓል።
በውይይቱ ኃላፊው ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወሳኝ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል የኒውክሌር ኃይል ጣቢያ ለመገንባት ሩሲያ ተገቢውን ትብብር ለማድረግ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት እንዳላት ገልፀዋል።
አምባሳደር ገነት በበኩላቸው ሀገራት የኃይል ማመንጨት አቅማቸውን በኒውክሌር ኃይል ሊያሰፉ እንደሚገባ አፅዕኖት በመስጠት፤ ሩሲያ በዚህ ረገድ ባለፉት ሰማንያ ዓመታት ያስመዘገበችውን ስኬት አድንቀዋል።
ስፓስኪ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የገንዘብ መዋጮ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ መመረቁንም አድንቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X