የዓለም ባንክ አፍሪካን ችላ በማለት ትኩረቱን በሙሉ ወደ ዩክሬን እንዳደረገ ተንታኙ ተናገሩ
10:50 20.09.2025 (የተሻሻለ: 10:54 20.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዓለም ባንክ አፍሪካን ችላ በማለት ትኩረቱን በሙሉ ወደ ዩክሬን እንዳደረገ ተንታኙ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የዓለም ባንክ አፍሪካን ችላ በማለት ትኩረቱን በሙሉ ወደ ዩክሬን እንዳደረገ ተንታኙ ተናገሩ
የዓለም ባንክ ከአፍሪካ ሀገራት ይልቅ ለዩክሬን ቅድሚያ መስጠቱ ባንኩ ወደ ምዕራባውያን ጂኦፖለቲካዊ ጥቅሞች ማዘንበሉን ያሳያል፤ ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የፍሪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የድህረ ዶክትሬት ባልደረባ ታፋዝዋ ሩዚቭ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዓለም ባንክ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ድምር በላይ ለዩክሬን ከፍተኛ ብድር መስጠቱ፤ የድህነት ቅነሳ እና ዘላቂ ልማት ግቦቹን ወደ ጎን እንዳለ ያሳያል ብለዋል።
"የዓለም ባንክ አጠቃላይ የዩክሬን ሀገርን ለዎል ስትሪት የገንዘብ አበዳሪዎቹ ጥቅም በዋስትና ለማስያዝ አፍሪካን ትቶ በዩክሬን ኢንቨስት እያደረገ ነው" ያሉት ዶ/ር ሩዚቭ፤ ብድሩ ለዩክሬን የሚፈሰው ከግጭቱ በኋላ የተፈጥሮ ሀብቶቿን እና የመንግሥት ንብረቶቿን ለመቆጣጠር ነው ሲሉም ሞግተዋል።
የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለአፍሪካ ሀገራት ደንታ ቢስ መሆናቸውን በመተቸት፤ እነዚህ ተቋማት "የአፍሪካን መሠረታዊ ችግሮች ለመፍታት ተጨንቀውም ፈልገውም አያውቁም" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X