የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አማፅያን መስጂድ ላይ ባነጣጠረ የድሮን ጥቃት፤ በርካቶችን እንደገደሉ የህክምና ቡድን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አማፅያን መስጂድ ላይ ባነጣጠረ የድሮን ጥቃት፤ በርካቶችን እንደገደሉ የህክምና ቡድን አስታወቀ
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አማፅያን መስጂድ ላይ ባነጣጠረ የድሮን ጥቃት፤ በርካቶችን እንደገደሉ የህክምና ቡድን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.09.2025
ሰብስክራይብ

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አማፅያን መስጂድ ላይ ባነጣጠረ የድሮን ጥቃት፤ በርካቶችን እንደገደሉ የህክምና ቡድን አስታወቀ

አማፂ ቡድኑ በሰሜን ዳርፉር፣ ኤል-ፋሸር ከተማ አቅራቢያ፤ አቡ ሹክ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ውስጥ በሚገኝ መስጂድ ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት፤ ቢያንስ 75 ሰዎች ተገድለዋል ሲል የሱዳን ዶክተሮች መረብ የተሰኘው የሲቪል ህክምና ተቋም ገልጿል፡፡

ዛሬ አርብ የተፈፀመው ጥቃት፤ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በዳርፉር የሱዳን ሠራዊት የመጨረሻ ይዞታ የሆነችውን ከተማ ለመቆጣጠር ጥቃቱን አጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት የመጣ ነው ተበሏል፡፡

ለ18 ወራት ያህል በከበባ ስር የቆየችው ኤል-ፋሸር፤ በክልሉ የሱዳን ጦር የመጨረሻ ቁልፍ ይዞታ ሆና ስታገለግል ቆይታለች።

የከተማዋ ከሱዳን ጦር እጅ መውጣት፤ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ቀድሞውንም አሰቃቂ ድርጊቶች ተፈፀመውበታል የሚባለውን የዳርፉር ክልል፤ ሙሉ በመሉ በቁጥጥሩ ስር እንዲያደርግ ያስችለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት፤ በዚህ ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ብቻ፤ አብዛኛው በዳርፉር፤ ከ3 ሺህ 384 በላይ ሲቪሎች ተገድለዋል ብሏል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0