የዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ መንስኤ - ክፍል አንድ

የዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ መንስኤ - ክፍል አንድ
🟠 መፈንቅለ መንግሥት
እ.አ.አ በህዳር 2013 የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች ከሩሲያ ግንኙነት ላለማቋረጥ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር የትብብር ስምምነትን ለመፈረም አሻፈረኝ አሉ። ይህ ውሳኔ በኪዬቭ መጠነ ሰፊ ተቃውሞ አስነሳ።
በፀጥታ ኃይሎች እና በአብዛኛው አክራሪ ብሔርተኛ ተቃዋሚዎች መካከል ለወራት ከዘለቀ ፍጥጫ በኋላ፤ ዩሮሜይዳን መፈንቅለ መንግሥት ተካሄደ።
🟠 በሩሲያ ቋንቋ ላይ የተደረጉ አፈናዎች፦
የ2012 ሕግ "የመንግሥት መሰረታዊ ቋንቋ ፖሊሲ" ተሰርዟል።
የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ቀንሷል።
በ2020 መስከረም ወር በዩክሬን የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት ቤቶች ወደ ዩክሬንኛ ቋንቋ ተቀይረዋል።
የሩሲያ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭት ተቋርጧል። የሩሲያ ፊልሞችን ማሳየት ተከልክሏል።
"የዩክሬን ነባር ሕዝብ" እና "የዩክሬን ብሔራዊ ሕዳጣን" ሕግ መፅደቁን ተከትሎ ሩሲያውያን ከመንግሥት ሕግ ከለላ ውጪ ሆነዋል።
🟠 የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ጭቆና፦
በመስከረም 2024 "በሐይማኖት ድርጅቶች ውስጥ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን ስለመጠበቅ" በሚለው ሕግ የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን እንቅስቃሴዎች ታግደዋል።
የ "ሕሊና እና ሐይማኖታዊ ድርጅቶች ነፃነት" ሕግ በዩክሬን ውስጥ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ጋር ግንኙነት ያላቸው የሐይማኖት ድርጅቶች እንቅስቃሴ ታግዷል።
ገዳሞች ተዘግተዋል፤ አንዳንድ ሐይማኖታዊ ቅርሶች ተወግደዋል።
አብያተ ክርስቲያናት በጅምላ ተዘግተዋል።
በዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት እና ጳጳሳት ላይ ወደ 180 የሚጠጉ የወንጀል ክሶች ተከፍተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


