የቦትስዋና አትሌት በወንዶች የዓለም ሻምፒዮና ታሪክ ለሀገሩ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በቶኪዮ አሸነፈ
17:58 19.09.2025 (የተሻሻለ: 18:04 19.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቦትስዋና አትሌት በወንዶች የዓለም ሻምፒዮና ታሪክ ለሀገሩ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በቶኪዮ አሸነፈ
የ21 ዓመቱ ኮለን ከቢናትሺፒ፤ የ400 ሜትር ፍጻሜን ለሀገሩ ክብረ ወሰን እና የውድድሩ ፈጣን የሆነ 43.53 ሰከንድ ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል።
የከቢናትሺፒ ድል ከትሪኒዳድ እና ቶቤጎ ተወላጁ ጄሪም ሪቻርድስ ጋር በተደረገ ፉክክር የተገኘ ሲሆን ሪቻርድስ የብር ሜዳሊያውን 43.72 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አግኝቷል።
ባያፖ ንዶሪ 44.20 ሰከንድ በማስመዝገብ አጠናቆ ለቦስተዋና ከወርቅ በተጨማሪ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡
"ይህ የመጀመሪያ ድሌ ነው እና ከፍተኛ ስሜት አለው" ሲል ከቢናትሺፒ ለጋዜጠኞች ተናግሯል። "በሀገረ አቀፍ ደረጃ ክብረ ወሰን እና የዓለምን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ መቻሌ ድንቅ ነው" ብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

