የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን በ19ኛው ዙር ማዕቀብ የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን ለዩክሬን ብድር በማስያዣነት ለመጠቀም ሀሳብ ማቅረቡን ኧርሰላ ቮን ደር ሌይን ተናገሩ
15:46 19.09.2025 (የተሻሻለ: 15:54 19.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን በ19ኛው ዙር ማዕቀብ የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን ለዩክሬን ብድር በማስያዣነት ለመጠቀም ሀሳብ ማቅረቡን ኧርሰላ ቮን ደር ሌይን ተናገሩ
እቅዱ ወደ አባል ሀገራቱ የሚገባውን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት እገዳንም እንደሚያካትት የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት አስታውቀዋል፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ገንዘብ በአውሮፓ መታገዱን በተደጋጋሚ ስርቆት ነው ሲል አውግዟል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሞስኮ በሩሲያ የምዕራባውያን ሀገራት ንብረቶችን በመከልከል ምላሽ ልትሰጥ ትችላለች ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር።
እ.ኤ.አ በ2022 ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች በኋላ የአውሮፓ ኅብረት እና የቡድን 7 ጥምረት በድምሩ 300 ቢሊዮን ዩሮ የሚገመተውንና ከሩሲያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ግማሽ ያህሉን አግደዋል።
የአውሮፓ ኅብረት የሩሲያን ንብረቶች ለመስረቅ የሚያደርገው ሙከራ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ላይ የከፋ አሉታዊ መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X