ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም የጀመረችውን እንቅስቃሴ እደግፋለሁ - ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ
14:26 19.09.2025 (የተሻሻለ: 14:34 19.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም የጀመረችውን እንቅስቃሴ እደግፋለሁ - ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም የጀመረችውን እንቅስቃሴ እደግፋለሁ - ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ
በኦስትሪያ ቪየና እየተካሄደ ካለው 69ኛው የኤጀንሲው መደበኛ ጉባኤ ጎን ለጎን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና ዋና ዳይሬክተሩ ራፋኤል ግሮሲ በኢትዮጵያ የኒውክሌር ቲክኖሎጂ ውጥን ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ ኤጀንሲው ብሔራዊ የኒውክሌር ኃይል ግንባታ ላይ የቴክኒክ እና የእውቀት ሽግግር ድጋፍ እንዲያደርግ መጠየቃቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም የሚያስችል መሠረት በመጣል ወደ ትግበራ ለመግበት ሰፊ ጥረት እያደረገች እንደሆነም አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የኢትዮጵያ የኒውክሌር መሠረተ ልማት በመገንባት ለዘርፈ ብዙ ዔላማ ለማዋል እንዳቀደች በ 'የመደመር መንግሥት' መፅሐፍ ምረቃ ወቅት ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X