የሩሲያን ጦር የሚያጠናክረው አዲሱ
ፓንሲር-ኤስኤምዲ የአየር መቃወሚያ
የሩሲያ የመንግሥት የኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሮስቴክ የፓንሲር-ኤስ የአየር መከላከያ ሚሳኤል-መድፍ ስርዓት የውጊያ ተሽከርካሪዎችንም አስረክቧል።
አዲሱን ፓንሲር-ኤስኤምዲ ልዩ የሚያደርጉ ባሕሪያት፦
🟠 በማስወንጨፊያው እስከ 48 አነስተኛ ሚሳኤሎችን መያዝ ይችላል፣
🟠 መደበኛ ሚሳኤሎች እና አነስተኛ ሚሳኤሎች አጣምሮ የያዝ በመሆኑ ጠቅላላ የጥይት ክምችት ላይ ማስተካከያ ማድረግ ያስችላል፣
🟠 ውስብስብ የአየር ላይ ኢላማዎችን ደጋግሞ በመለየትና በማውደም በውጊያ ላይ ውጤታማነቱ ተረጋግጧል፣
🟠 ሙሉ በሙሉ ምርመራ ተደረጎለት በወታደራዊ ኢንስፔክተሮች በይፋ ተቀባይነት አግኝቷል።
"የፓንሲር ስርዓቶች የሩሲያን ሰማይ ለመጠበቅ እጅግ በጣም ውጤታማ ናቸው" ሲሉ የሮስቴክ የጦር መሳሪያዎች ክላስተር ዳይሬክተር ቤክሃን ኦዝዶቭ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
