የዓለም ባንክ የምዕራባውያን መሣሪያ በመሆን በዩክሬን ጦርነት እያገለገለ ነው - የምጣኔ ሃብት ባለሙያው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዓለም ባንክ የምዕራባውያን መሣሪያ በመሆን በዩክሬን ጦርነት እያገለገለ ነው - የምጣኔ ሃብት ባለሙያው
የዓለም ባንክ የምዕራባውያን መሣሪያ በመሆን በዩክሬን ጦርነት እያገለገለ ነው - የምጣኔ ሃብት ባለሙያው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.09.2025
ሰብስክራይብ

የዓለም ባንክ የምዕራባውያን መሣሪያ በመሆን በዩክሬን ጦርነት እያገለገለ ነው - የምጣኔ ሃብት ባለሙያው

አበዳሪ ተቋሙ ባለፉት ሦስት ዓመታት በአጠቃላይ ለአፍሪካ ከለቀቀው የአነስተኛ ወለድ ብድር አስራ ሁለት እጥፍ ለዩክሬን እንዳበደረ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን የሰጡት ኢትዮጵያዊው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ባንኩ በዩናይትድ ስቴትስ እና አውሮፓውያን ቁጥጥር ውስጥ እንደሆነ ገልፀዋል።

"የእነዚህ ድርጅቶች ዋና ዋና ባለድርሻዎች ድርጅቱ የሚሠራውን የሚወስኑ ናቸው። ዩክሬን ብዙ የሰብዓዊ እርዳታ እና የዓለም ባንክ ብድር የምታገኝበት ዋና ምክንያት በምዕራባውያን ተጽዕኖ እና የዩክሬን ጦርነትን ለመደገፍ ምዕራባውያን የፈጠሩት የኃይል አካል ስለሆነ ነው" ብለዋል።

ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ አክለውም የአፍሪካ እና የደቡባዊው ዓለም ሀገራት እነዚህ ከተጠያቂነት ነፃ ሆነው የቆዩት ተቋማት እንዲሻሻሉ ሲጎተጉቱ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0