የግብፅ ፈርዖን አምባር ከካይሮ ሙዚዬም መጥፋቱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየግብፅ ፈርዖን አምባር ከካይሮ ሙዚዬም መጥፋቱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ
የግብፅ ፈርዖን አምባር ከካይሮ ሙዚዬም መጥፋቱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.09.2025
ሰብስክራይብ

የግብፅ ፈርዖን አምባር ከካይሮ ሙዚዬም መጥፋቱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ

3 ሺህ ዓመት ዕድሜ ያስቆጠረው እና የፈርዖን አምነምኦፔ እንደሆነ የታመነው አምባር ካይሮ ከሚገኘው የግብፅ ሙዚዬም ላብራቶሪ ውስጥ መጥፋቱን የቱሪዝም እና የቅርስ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።

"ሚኒስቴሩ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው አካላትና ለሕዝብ እንዲሁም ለአቃቤ ሕግ መርቶ በቤተ ሙከራው ውስጥ ያሉትን ዕቃዎች በዝርዝር ለመመዝገብ ልዩ ኮሚቴ አቋቁሟል። የአምባሩ ምሥል በግብፅ አውሮፕላን ማረፊያዎችና ድንበሮች በሚገኙ የቅርስ ክፍሎች በሙሉ ተሰራጭቷል" ሲል መግለጫው ጠቅሷል፡፡

ከብረትና ከላፒስ ላዙሊ የተሠራው ቅርስ የጠፋው በእድሳት ወቅት መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ፎቶዎች የጠፋውን አምባር እንደማያሳዩም ጠቁሟል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየግብፅ ፈርዖን አምባር ከካይሮ ሙዚዬም መጥፋቱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ
የግብፅ ፈርዖን አምባር ከካይሮ ሙዚዬም መጥፋቱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.09.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0