የሩሲያ አውሮፕላን ሞተሮች ከሀገሪቱ ተወዳዳሪ ብልጫ መውሰጃዎች መካከል ናቸው - ፑቲን
18:45 18.09.2025 (የተሻሻለ: 18:54 18.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ አውሮፕላን ሞተሮች ከሀገሪቱ ተወዳዳሪ ብልጫ መውሰጃዎች መካከል ናቸው - ፑቲን
የሩሲያው ፒዲ-14 የአውሮፕላን ሞተር ከዓለም አቀፍ ደረጃዎች የላቀ ነው ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል፡፡ ሩሲያን ጨምሮ በዓለም ላይ አራት ሀገራት ብቻ ከፒዲ-14 ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ሞተሮችን እንደሚያመርቱ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ሩሲያ የጦር ኃይሉን የውጊያ አውሮፕላን ፍላጎቶች ሙሉ በሙሉ ታሟላለች እንዲሁም ለወጪ ንግድ አቅርቦቶችን ትልካለች ሲሉ በስቴት ዱማ ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ሩሲያ የውጊያ አውሮፕላን ምርት ኢንዱስትሪን አድናለች፣ መልሳ አቋቁማለች እና ብዙ እርምጃዎችን ወደፊት አራምዳለች ያሉት ፑቲን፤ በሀገር ውስጥ ሞተር ግንባታም ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X