የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ማጠናከሪያ የ400ሺ ዶላር ድጋፍ ሰጠ
17:02 18.09.2025 (የተሻሻለ: 17:04 18.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ማጠናከሪያ የ400ሺ ዶላር ድጋፍ ሰጠ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ማጠናከሪያ የ400ሺ ዶላር ድጋፍ ሰጠ
በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን ለሕዝብ ክፍት ማድረግ የሚያስችል መድረክ ለመገንባት፣ በአክሲዮን ገበያ የሚሸጡ ፈንዶችንና የፋይናንስ ዘርፉ አዳዲስ ግብዓቶችን ለማስተዋወቅ የተደረገ ድጋፍ ነው ተብሏል፡፡
የሕዝብ መረጃ መግለጫ ሥርዓቱ፦
የኩባንያ መረጃን ለባለሀብቶች፣ ለአክሲዮን ባለቤቶች እና ለሌሎች የገበያ ተሳታፊዎች በወቅቱ እና በትክክል ማሠራጨት፣
በአክሲዮን ልውውጥ ገበያዎች ሊገዙ እና ሊሸጡ የሚችሉ የኢንቨስትመንት ፈንዶችን ማስተዋወቅ፣
ሸሪአን መሠረት ያደረጉ የፋይናንስ መሳሪያዎችን ማሳወቅ፣
አዳዲስ እና የተለያዩ የምርት አቅርቦቶችን ለገበያው ተደራሽ ማድረግን ያለመ ነው።
“ለኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ዘርፍ ልማት እና አቅም ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ፤ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፋጠን እና ወሳኝ የረዥም ጊዜ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት ቁልፍ ሚና ይጫወታል” ሲሉ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X