የመንግሥት የወጪ ቅነሳ ፖሊሲ በቃን ያሉ ተቃዋሚዎች በፈረንሳይ የተለያዩ ከተሞች ድምፃቸውን ለማሰማት ወጡ፤ ከፖሊስ ጋር መጋጨት መጀመራቸውም ተዘግቧል
የመንግሥት የወጪ ቅነሳ ፖሊሲ በቃን ያሉ ተቃዋሚዎች በፈረንሳይ የተለያዩ ከተሞች ድምፃቸውን ለማሰማት ወጡ፤ ከፖሊስ ጋር መጋጨት መጀመራቸውም ተዘግቧል
የፈረንሳይ የንግድ ማህበራት “ኢሰብዓዊ” ተብለው የተገለጹትን የበጀት እርምጃዎች በመቃወም ሀገር አቀፍ የሥራ ማቆም አድማ እና ሰልፎች እንዲደረጉ ጥሪ አቅርበዋል።
አሁናዊ መረጃዎች፦
▪ፖሊስ ሐሙስ ጠዋት በመላው ፈረንሳይ 476 ሰልፎች ተካሂደዋል ሲል አስታውቋል፣
▪135 እገዳዎች ተመዝግበዋል፣ 11 ተነስተዋል፣
▪እስከ እኩለ ቀን ድረስ 94 ሰዎች ታስረዋል፤ 15ቱ በፓሪስ እና 32 ሰዎች በግዜያዊ እስር ላይ ይገኛሉ፣
▪ ከ800 ሺህ በላይ ሰልፈኞች እንደሚወጡ ይጠበቃል፣
▪80 ሺህ ፖሊሶች እና የጸጥታ አካላት በድሮኖች እና በውሃ አድማ መበተኛዎች ታግዘው ተሰማርተዋል ሲሉ ሥልጣናቸውን የለቀቁት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ሬታይሎ ተናግረዋል፣
▪22 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዘገተዋል ወይም ለመዝጋት ተሞክሯል፤ ዛሬ ሁሉም ፋርማሲዎች ማለት ይቻላል የሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው፣
▪የሕዝብ ትራንስፖርት በተለይም በፓሪስ ተስተጓጉሏል ተብሏል፣ አብዛኞቹ የምድር ውስጥ ባቡሮች እና የከተማ ዳርቻ ባቡሮች ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ባለበት ሰዓት ላይ ብቻ አገልግሎት ይሰጣሉ፣
▪ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች የዩሮሊንክ የጦር መሳሪያዎች ፋብሪካን ዘግተዋል፤ ይህ ፋብሪካ ለእስራኤል አነስተኛ ጥይቶችን በማምረት ይታወቃል ሲሉ የፈረንሳይ ፓርላማ አባል ተናግረዋል፣
▪የኤስዩዲ የባቡር ዘርፍ የሠራተኛ ማህበር አባላት በፓሪስ በርሲ የሚገኘው የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስቴርን ተቆጣጥረዋል፣
▪ሥልጣናቸውን የለቀቁት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር በማርቲኒክ የውሃ አውታርን ለ “ማበላሸት” የተደረገው ሙከራ ከሽፏል ብለዋል፣
▪በሊዮን እና ናንትስ ግጭቶች ተቀስቅሰዋል፤ ፖሊስ ጥቃት ከደረሰበት በኋላ በአስለቃሽ ጭስ ጋዝ ምላሽ ሰጥቷል። በሊዮን አንድ የፖሊስ አባልን ጨምሮ ሶስት ሰዎች ቆስለዋል።
ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምሥሎች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X