ኢትዮጵያዊው ደራሲ አበረ አዳሙ ለብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ታጩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያዊው ደራሲ አበረ አዳሙ ለብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ታጩ
ኢትዮጵያዊው ደራሲ አበረ አዳሙ ለብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ታጩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያዊው ደራሲ አበረ አዳሙ ለብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ታጩ

የእጩዎች ዝርዝሩ በብራዚሊያ በተካሄደው ሁለተኛው የብሪክስ የባሕላዊ እሴቶች ጉባኤ ላይ ይፋ ተደርጓል።

በዝርዝሩ ከብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ግብፅ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ኢራንና ኢንዶኔዥያ ጨምሮ ከሌሎችም ሀገራት የተወጣጡ 27 ደራሲያን ተካተውበታል፡፡

በብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ዙሪያ በተካሄደው ውይይት ወቅት፤ የሥነ ጽሑፍ ምሁራንና አሳታሚዎችን የሚያካትት የብሪክስ ሀገራት የጸሐፊዎች ማኅበር ምሥረታም እውን ሆኗል፡፡ የማኅበሩ ዋነኛ ዓላማ ቀጣይነት ያለው የባሕል ልውውጥን ማሳደግ እና በሥነ ጽሑፍ መስክ የሚደረጉ ጥረቶችን ማስተባበር እንዲሁም የሽልማቱን አዘጋጅ ኮሚቴ መደገፍ ነው።

“የብሪክስ ሥነ ጽሑፍ ሽልማት ስለ ሀገራቸው ባሕልና ወጎች ለሚጽፉና ዕውቀትን ለሚያሰራጩ ደራሲያን ልዩ ዕድል ነው። የዚህ ሽልማት ሀሳብ ተሳታፊ ሀገራት በባሕላቸውና በወጋቸው መነፅር አማካኝነት እርስ በእርሳቸው በተሻለ ሁኔታ እንዲተዋወቁ ነው፤ ምክንያቱም ሥነ ጽሑፍ የሀገራትን ታሪክና ወግ ለማቆየት ወሳኝ መሣሪያ ነው” ሲሉ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የሽልማቱ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል ዘለዓለም መልዐክ ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0