ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ድጋፉን እንዲያጠናከር ጥሪ ቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ድጋፉን እንዲያጠናከር ጥሪ ቀረበ
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ድጋፉን እንዲያጠናከር ጥሪ ቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ድጋፉን እንዲያጠናከር ጥሪ ቀረበ

በኦስትርያ ቬና እየተካሄደ በሚገኘዉ 69ኛው የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ፤ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ለሆነ ሀገራዊ እድገት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫን በመገንባት ለመጠቀም ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የኢትዮጵያ የኒውክሌር መሠረተ ልማት የመገንባት ውጥን ለዘርፈ ብዙ አላማ ለማዋል ያለመ እንደሆነ በ 'የመደመር መንግሥት' መፅሐፍ ምረቃ ወቅት ተናግረዋል።

ለኃይል አቅርቦት፣

ለምርምር፣

ለጤና፣

ለግብርና፣

ለኢንዱስትሪ፣

ለአካባቢ ጥበቃ እንደሚውልም ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ እ.አ.አ ከ1957 ጀምሮ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አባል ሀገር መሆኗ ይታወቃል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0