የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ መደገፋቸው ለኢኮኖሚ እና የደህንነት ጉዳዮች ቅድሚያ መስጠታቸውን የሚያንፀባርቅ ነው - የፖለቲካ ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሶማሊያ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ መደገፋቸው ለኢኮኖሚ እና የደህንነት ጉዳዮች ቅድሚያ መስጠታቸውን የሚያንፀባርቅ ነው - የፖለቲካ ተንታኝ
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ መደገፋቸው ለኢኮኖሚ እና የደህንነት ጉዳዮች ቅድሚያ መስጠታቸውን የሚያንፀባርቅ ነው - የፖለቲካ ተንታኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.09.2025
ሰብስክራይብ

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ መደገፋቸው ለኢኮኖሚ እና የደህንነት ጉዳዮች ቅድሚያ መስጠታቸውን የሚያንፀባርቅ ነው - የፖለቲካ ተንታኝ

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ የኢትዮጵያን ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ የባሕር በር ጥያቄ እንደሚደገፉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን የሰጡት የፖለቲካ ተንታኙ ሚካኤል ማስሬ፤ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያ ተዓማኒነት እና የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ተፅዕኖ እንዲጨምር ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት በመላክ የቀጣናው የኃይል ማዕከል መሆኗ፤ የኢኮኖሚ ውህደትን እንደሚያጠናክር እና እንደ ሶማሊያ ያሉ ሀገራት ትብብር እንዲመርጡ እንደሚያነሳሳቸው ተናግረዋል፡፡

"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቅርቡ በሕዳሴ ምረቃ ላይ መሪዎች የሀገሪቱን ራዕይ እንዲቀላቀሉ በመጠየቅ፤ ከአጸፋዊ ይልቅ አዎንታዊ እና የተረጋጋ ዲፕሎማሲ አሳይተዋል። የሶማሊያን ፕሬዝዳንት ምልክት ከእዚህ ጋር ማገናኘት እንችላለን። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግር አንድ ጠቃሚ ነገር ወስደዋል ብዬ አምናለሁ። ከፖለቲካ አንፃር ጥሩ ምልክት ነው” ብለዋል፡፡

የተረጋጋ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ግንኙነት ለቀጣናው ሰላምና እንደ ኢጋድ እና የአፍሪካ ኅብረት ላሉ ድርጅቶች መጠናከር ወሳኝ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0