ኢትዮጵያ በሰላማዊ እና በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ትቀጥላለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
12:28 18.09.2025 (የተሻሻለ: 12:34 18.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በሰላማዊ እና በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ትቀጥላለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና እንደማትቀጥል አፅዕኖት በመስጠት፤ ጥያቄው የመብት፣ የልማት እና የመጪውን ትውልድ መፃኢ እድል የተመለከተ እንጂ የጦርነት አይደለም ብለዋል፡፡
“ይህን ለማሳካት ጦርነት እና ግጭት አስፈላጊ ነው ብለን አናምንም፤ ለዚህም ነው አምስት ዓመት ሙሉ በትዕግስት የጠበቀነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከመቼውም ግዜ በላይ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት እጇን ዘርግታለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት ፅኑ እምነት አለን ሲሉ አስረግጠዋል፡፡
የታጠረ ምድርን ለልጆቻችን ማውረስ የለብንም ለዚህም ሁሉም ዜጋ የባሕር በር በማግኘት ሂደቱ ላይ በጋራ ሊቆም ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X