የጨረር ሕክምና ማሽን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሊተከል ነው
19:45 17.09.2025 (የተሻሻለ: 19:54 17.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የጨረር ሕክምና ማሽን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሊተከል ነው
የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ከቫሪየን (ሲመንስ ህልዝይነርስ ኩባንያ) በልገሳ ያገኘውን የጨረር ሕክምና መስጫ ማሽን ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ማሪያኖ ግሮሲ፣ በሐምሌ ወር በሆስፒታል ባደረጉት ጉብኝት የጨረር ሕክምና አገልግሎትን በአስቸኳይ ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ መመልከታቸውን ተከትሎ የተደረገ ድጋፍ ነው፡፡
"ከቫሪየን የተገኘው ልገሳ የካንሰር ሕክምናን ለሁሉም ለማዳረስ፤ ለአንድ ዓላማ መተባበር ያለውን ተፅእኖ ያሳያል፡፡ በጋራ በመሥራት ሕይወት አድን ቴክኖሎጂዎች በአፋጣኝ ለሚያስፈልጋቸው ማኅበረሰብ ክፍሎች ማዳረስ እንችላለን።" ብለዋል፡፡
አዲሱ ማሽን ለኢትዮጵያውያን ሕይወት አድን የካንሰር ሕክምና የማዳረስ አቅምን በማጎልበት እና በመላው አፍሪካ ተግባራዊ የተደረገውን “የተስፋ ጨረር” ንቅናቄ ለማሳደግ ይረዳል ተብሏል።
እ.አ.አ በ2045 በኢትዮጵያ 176 ሺህ አዳዲስ የካንሰር ሕሙማን እና 122 ሺህ ሞት ሊመዘገብ እንደሚችል በመተንበይ ድጋፉ ይህን ጫና ለማቃለል ይረዳል ሲል ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/