ግዙፉ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የላቀ አበርክቶ ይኖረዋል - የምጣኔ ሐብት ባለሙያ

ሰብስክራይብ

ግዙፉ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የላቀ አበርክቶ ይኖረዋል - የምጣኔ ሐብት ባለሙያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊ ገቢ በቀጣይ 15 ዓመታት ወደ 40 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያድግ የተቀመጡ ትንበያዎችን ዕውን ለማድረግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የሲቢኢ ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዘመዴነህ ንጋቱ ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ መንግሥት ለግንባታው ብልህ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስልቶችን መከተሉን አንስተዋል።

"የአፍሪካ ልማት ባንክ ለፕሮጀክቱ የፋይናንስ አስተባባሪነት ተመርጧል። ነገር ግን ሌሎች በርካታ ትላልቅ የአውሮፓ፣ የአሜሪካ፣ የእስያ፣ የባሕረ ሰላጤው እና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ባንኮችም እዚህ ተገኝተዋል። የመጡት እንደ ገንዘብ ድጋፍ እድራጊ እንጂ እንደ ባለድርሻ አይደለም" ብለዋል።

በ10 ቢሊየን ዶላር ወጪ በሁለት ምዕራፍ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያው በ10 ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0