አሁን ላይ ለትራምፕ እና ፑቲን ውይይት የተያዘ ቀጠሮ የለም - ክሬምንሊን

አሁን ላይ ለትራምፕ እና ፑቲን ውይይት የተያዘ ቀጠሮ የለም - ክሬምንሊን
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪቭ ፔስኮቭ ቁልፍ መግለጫዎች፦
🟠 በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ያሉ ግንኙነቶች በተለያዩ መንገዶች ይቀጥላሉ፡፡
🟠 ሩሲያ እና አሜሪካ የከፍተኛ ደረጃ ግንኙነቶችን በፍጥነት ለማደራጀት እድሉ አላቸው፡፡
🟠 ሩሲያ በዩክሬን ድርድር ሂደት ላይ ያላት ዝግጁነት ታስቀጥላለች፡፡
🟠 ለሩሲያ በዩክሬን ያለውን ሁኔታ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍታት ተመራጭ ነው፡፡
🟠 ሩሲያ ብሔራዊ ጥቅሟን ታስጠብቃለች፤ እናም ለአውሮፓውያን ማዕቀቦች ተጽዕኖ አትጋለጥም፤ 18ቱ የአውሮፓ ሕብረት ማዕቀብ ጥቅሎች ይህንን አሳይተዋል።
🟠 ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የማሻሻያ ሐሳብን ያለማቋረጥ ትደግፋለች፡፡
🟠 የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ማድረግ የሚቻለው በስምምነት ብቻ ነው፡፡ አሁን ግን በቋሚ አባላት መካከል አለመግባባት በመኖሩ የማይቻል ነው፡፡
🟠 ሩሲያ እና አጋሮቿ የተባበሩት መንግሥታትን ያማከለ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥርዓት በዓለም ላይ እንዲኖር ይታገላሉ፡፡
🟠 አውሮፓ ተከታታይነት ያለው የማዕቀብ ጫና የሩስያ ፖሊሲ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል ብላ ማመኗ ስህተት ነው፡፡
🟠 ፑቲን የተመለከቱት የዛፓድ-2025 የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በመጠኑ አስደናቂ ነበር፡፡
🟠 ፑቲን መሻሻሎችን እና የዛፓድ-2025 ወታደራዊ ልምምድ ውጤትን በጥሩ እና በከፍተኛ ሁኔታ ገምግመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X