የትራምፕን የብሪታንያ ጉብኝት የሚቃወም ሕዝባዊ ሰልፍ በማዕከላዊ ለንደን ተጀመረ
17:35 17.09.2025 (የተሻሻለ: 17:44 17.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የትራምፕን የብሪታንያ ጉብኝት የሚቃወም ሕዝባዊ ሰልፍ በማዕከላዊ ለንደን ተጀመረ
ከማዕከላዊ ጎዳናዎች በአንዱ መሰብሰብ የጀመሩት ተቃዋሚዎች በመቀጠልም በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሰልፍ ወደሚደረግበት ፓርላማ አደባባይ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል።
ሰልፈኞች “ትራምፕ ይውደቅ”፣ “እምቢ ለዘረኝነት፣ እምቢ ለትራምፕ”፣ “ትራምፕን እናስቁም”፣ “የትራምፕ ኒዩክሌር ቦንብ አስቁሙ” እና “በጋዛ የዘር ማጥፋት ይቁም” የሚሉ መፈክሮችን እንዲሁም ትራምፕን የሚነኩ የሽሙጥ አስቂኝ ምስሎችን ይዘው ተገኝተዋል።
"ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር በሀገራችን ያሉ ትክክለኛ ችግሮችን ለመፍታት ምንም ነገር ሳያደርጉ ሀገራችንን ለኮርፖሬት ቁጥጥር ክፍት ለሚያደረገው የቴክኖሎጂ ውል ብሪታንያን እየሸጡ ነው፤ " ሲሉ የሰልፉ አዘጋጆች ተናግረዋል ።
ትራምፕ በለንደን ስላልሆኑ ሰልፉን ማየት አይችሉም የተባለ ሲሆን የፕሬዚዳንቱ የአካሄድ መንገድ በተለይ ተቃውሞዎችን ለመሸሽ የታቀደ ነበር ሲል የአሜሪካ ጋዜጣ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

