ከፀጥታ ወደ ሆታ፤ አዲስ አበባ ስቴዲየም ከ5 ዓመት በኋላ የሊግ ውድድሮችን ሊያስተናግድ ነው
17:15 17.09.2025 (የተሻሻለ: 17:24 17.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከፀጥታ ወደ ሆታ፤ አዲስ አበባ ስቴዲየም ከ5 ዓመት በኋላ የሊግ ውድድሮችን ሊያስተናግድ ነው
የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ የስፖርት ውድድሮች በስፖርታዊ ጨዋነት ማጠናቀቅ የውድድሮች ቅድመ ሁኔታን መሆኑን በማሳሰብ፣ ስቴዲየሙ ለጨዋታ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“መንግሥት ለስፖርት ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ለዓመታት ጥገና እና እድሳት ላይ የነበረውን የአዲስ አበባ ስታዲየም በማጠናቀቅ ውድድሮችን ለማስተናገድ ዝግጁ እንደሆነ” ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጂራ፣ ባለፉት ዓመታት ፕሪሚየር ሊጉ በተመረጡ ስታዲየሞች እና ከተሞች ብቻ በመደረጉ በተለይ ተመልካች ከሜዳ እንዲርቅ መኾኑ እና ክለቦችም በፋይናንስ ደረጃ የሚገባቸውን እንዳያገኙ መኾናቸው ተጠቁሟል።
በ2018 ዓ.ም ፕሪሚየር ሊጉን በዙር በሜዳ እና ከሜዳ ውጭ ለማድረግ የታቀደ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


