ሰርጌ ሾይጉ ስለ ደኅንነት፣ የመካከለኛ ምስራቅ ውጥረትና የሩስያ አረብ መሪዎች ጉባኤ ላይ በባግዳድ ውይይት አደረጉ፡፡

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሰርጌ ሾይጉ ስለ ደኅንነት፣ የመካከለኛ ምስራቅ ውጥረትና የሩስያ አረብ መሪዎች ጉባኤ ላይ በባግዳድ ውይይት አደረጉ፡፡
ሰርጌ ሾይጉ ስለ ደኅንነት፣ የመካከለኛ ምስራቅ ውጥረትና የሩስያ አረብ መሪዎች ጉባኤ ላይ በባግዳድ ውይይት አደረጉ፡፡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.09.2025
ሰብስክራይብ

ሰርጌ ሾይጉ ስለ ደኅንነት፣ የመካከለኛ ምስራቅ ውጥረትና የሩስያ አረብ መሪዎች ጉባኤ ላይ በባግዳድ ውይይት አደረጉ፡፡

የሩስያ ደኅንነት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ በጉብኘታቸው ከኢራቁ ፕሬዝዳንት አብዱል ላቲፍ ራሺድ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ አለሱዳኒ፣ ከመከላከያ ሚኒስትሩ ታሕቢት አልአባሲ ጋር መወያየታቸውን ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

🟠 ውይይት እና ደኅንነት፦ ሾይጉ በሩስያ እና በኢራቅ መካከል በተለይም በደኅንነት ምክር ቤት አማካይነት የሁለተዮሽ ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።

🟠 የሩስያ አረብ መሪዎች ጉባኤ፦ ሾይጉ ትብብርን እንደሚያሳድግ ያላቸውን እምነት የገለፁበት፣ በጥቅምት አጋማሽ በሞስኮ የሚካሄደው የሩስያና የአረብ ሀገራት መሪዎች ጉባኤም የውይይታቸው አካል ሆኗል፡፡

🟠 የመካከለኛው ምስራቅ ስጋቶች፦ ሾይጉ የእስራኤል እና የፍልስጤምን ግጭት በተለይም እስራኤል በዶሃ ላይ የፈፀመችውን ጥቃት እና ይዞት የሚመጣው መዘዝ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ በጋዛ ያለው ጥቃት እንዲቆም አሳስበዋል። በሶሪያ፣ ሊባኖስና የመን ያሉ ውጥረቶችንም አንስተዋል።

🟠 ወታደራዊ ትብብር፦በሩሲያ እና ኢራቅ መካከል በሚኖረው በወታደራዊ-ቴክኒካል ትብብር ላይም ተወያይተዋል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0