ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሕንዱ ጥቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር የስልክ ንግግር አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሕንዱ ጥቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር የስልክ ንግግር አደረጉ
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሕንዱ ጥቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር የስልክ ንግግር አደረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.09.2025
ሰብስክራይብ

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሕንዱ ጥቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር የስልክ ንግግር አደረጉ

ዛሬ ማለዳ ፑቲን 75ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው ለሚያከብሩት ሞዲ ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርበዋል፡፡

የሩሲያው ፕሬዝዳንት "በአገሮቻችን መካከል ያለውን ልዩ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማጠናከር እና በተለያዩ ዘርፎች የጋራ ተጠቃሚነት ያለውን የሩሲያ እና ሕንድ ትብብር ለማሳደግ በግልዎ ትልቅ አበርክቶ እያደረጉ ነው" ሲሉ በእንኳን አደረሰዎት መልእክታቸው ገለፀዋል፡፡

ሕንድ በሞዲ አመራር ስር በማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሳይንሳዊ እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ሁሉ ያስመዘገበቻቸውን "አስደናቂ ስኬቶች" አሞካሽተዋል፡፡ እንዲሁም በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ትብብርን ለማጠናከር የሩሲያን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ፑቲን የስልክ ንግግር ከማድረጋቸው አስቀድሞ ዛሬ ጠዋት ለሞዲ "መልካም ጤንነት፣ ደስታ፣ ብልጽግና እና አዳዲስ ስኬቶች" ተመኝተውላቸዋል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0