ሶማሊያ የኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ እንደምትደግፍ አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሶማሊያ የኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ እንደምትደግፍ አስታወቀች
ሶማሊያ የኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ እንደምትደግፍ አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.09.2025
ሰብስክራይብ

ሶማሊያ የኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ እንደምትደግፍ አስታወቀች

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የኢትዮጵያን የባሕር በር የመፈለግ መብት እንደሚደገፉ መናገራቸውን ከአል አረቢያ ቲቪ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

"የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በዓለም አቀፍ ሕግ ማዕቀፍ ውስጥ አዲስ አይደለም፤ ማንኛውም ሀገር ዓለም አቀፍ ሕግጋት እና አኅጉራዊ ስምምነቶችን እስካከበረ ድረስ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ሊጠቀምባቸው የሚችላቸው እውቅና ያላቸው ዘዴዎች እና አካሄዶች አሉ" ብለዋል

ኢትዮጵያ ሕጋዊ መንገዶችን ከተከተለች ማሳካት እንደምትችልና ድጋፋቸውን እንደሚሰጡም ተናግረዋል፡፡

"በቀይ ባሕር አዋሳኝ አገሮች፣ የጸጥታና የኢኮኖሚ ፍላጎት ያላቸው አገሮች መረጋጋትን በሚያመጡና ሁሉንም የሚያገለግሉ የጋራ መግባባቶች እንዲፈጠሩ በውይይት፣ በመግባባትና ትብብር ላይ ሲሰሩ ይገባል፡፡" ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለውም የሶማሊያ አቋም ጽኑ እና ግልጽ ነው ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0