አውሮፓ በዩክሬን የድርድር ጠረጴዛ ላይ ቦታ ለማግኘት እየሞከረች ነው፤ ምንም እንኳን እዚያ ቦታ ባይኖራትም ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

አውሮፓ በዩክሬን የድርድር ጠረጴዛ ላይ ቦታ ለማግኘት እየሞከረች ነው፤ ምንም እንኳን እዚያ ቦታ ባይኖራትም ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዩክሬን ቀውስ ዙሪያ በተካሄደው የአምባሳደሮች ክብ ጠረጴዛ ስብሰባ ላይ የሰጧቸው ዋና ዋና መግለጫዎች፦

▪ኪዬቭ እና አውሮፓ ትራምፕ በዩክሬን ያለውን የሰላም ማስከበር ጥረት እንዲያቆሙ ለማሳመን እየሞከሩ ነው እንዲሁም የእልባት ሂደቱን ማደናቀፍ ይፈልጋሉ፡፡

▪የዩክሬን ግጭት እልባትን በተመለከተ ወቅታዊውን የአሜሪካን አቋም ለመጥለፍ እና በምዕራቡ ዓለም ያሉ "ጤናማ ኃይሎች" ይህንን አካሄድ እንዳይከተሉ ለመከላከል እየሞከረች ነው፡፡

▪ዩክሬን እና ምዕራባውያን ደጋፊዎቿ ሩሲያ ሲቪል ኢላማዎችን አነጣጥራለች በማለት በጮሁ ቁጥር፣ የተባበሩት መንግሥታት ጽሕፈት ቤት ያንን በማስተጋባት ሞስኮ እንድትቀጣ ይጠይቃል። ሆኖም የሩሲያ ጦር ሲቪሎችን ወይም ሲቪል መሠረተ ልማቶችን አያነጣጥርም፤ በፍጹም አድርጎ አያውቅም፡፡

▪የተባበሩት መንግሥታት ዩክሬንን እየተከላከለ እና የኪዬቭን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግጋትን የሚጥሱ ድርጊቶችን ችላ እያለ ነው።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0