ሀንጋሪ ከሩስያ የነዳጅ ግዢን ማቆም ላይ እንደማትስማማ አስታወቀች
11:45 17.09.2025 (የተሻሻለ: 11:54 17.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሀንጋሪ ከሩስያ የነዳጅ ግዢን ማቆም ላይ እንደማትስማማ አስታወቀች
እውነተኛ አማራጭ በሌለበት ከሩስያ የነዳጅ ግዢን መቀነስ የሀንጋሪን የኃይል ደህንነት ያወድማል ሲሉ የአውሮፓ ጉዳዮች ሚኒስተሩ ጃኖስ ቦካ ተናግረዋል፡፡
የሀንጋሪ መንግሥት የሀንጋሪን የአቅርቦት ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥል መፍትሄ ላይ በፍፁም አይስማማም፡፡ ሲሉ ቦካ በብራሰልስ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል፡፡
የሩስያ ኢኮኖሚ ለሀንጋሪ አልያም ለስሎቫኪያ በሚደረገ የነዳጅ ዘይት አቅርቦት ላይ የተመሠረት አይደለም ሲሉም ጠቁመዋል፡፡
የሩስያን ኢኮኖሚ እያስቀጠሉ ያሉት ሀንጋሪ እና ስሎቫኪያ ናቸው ብዬ አላስብም፡፡ ብለዋል
ሩሲያ የማዕቀቡን ጫና እንደምትቋቋም ደጋግማ ስታሳውቅ፣ ምዕራባውያን የማዕቀቡን የፖሊሲ ውድቀት ለመቀበል ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ጠቁማለች። ከዚህም በላይ የምዕራባውያን ባለሥልጣናት ማዕቀቡ ውጤታማ ባለመሆኑ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X