በመጨረሻም – ጉቴረዝ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እንዲሻሻል ጠየቁ
11:11 17.09.2025 (የተሻሻለ: 11:14 17.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በመጨረሻም – ጉቴረዝ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እንዲሻሻል ጠየቁ
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴረዝ፣ ይህ ሙሉ ስሜት የሚሰጥ (አሳማኝ) ነገር ነው ሲሉ አምነዋል፡፡
እርሳቸው እንዳመለከቱት፣ የፀጥታው ምክር ቤት አወቃቀር የ1945ቱን እንጂ የዘመናዊውን ዓለም እውነታን የሚያንፀባርቅ አይደለም። ይህም የድርጅቱን ቅቡልነት እና ውጤታማነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ይፈጥራል።
ሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት የአሁኑን ዓለም አቀፍ እውነታ እንደማያንፀባርቅ እና በዛሬው ኢኮኖሚ እና ጂኦፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያላቸውን ሀገራት እንደሚያገልል ደጋግማ በመግለጽ እንዲሻሻል ጥሪ አቅርባለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X